ወደ የኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር (ኢአማ) እንኳን በደህና መጡ!

ኢአማ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ህግ መሰረት የተመዘገቡ እና በየጊዜው ዘገባዎችን ለህዝብ የሚያቀርቡ የህትመት ፣ የበይነ-መረብ እና የስርጭት መገናኛ ብዙሃን ውስጥ በሚሰሩ አርታኢያን የተመሰረተ የሙያ ማህበር ነው፡፡ ማህበራችን ዋና አላማው ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ እና የመረጃ ነፃነት በኢትዮጵያ እንዲከበር ፣ የህግ ማዕቀፎች እንዲሁም የአፈፃፀም ሂደቶች እንዲሻሻሉ ውጤታማ ውትወታ ማድረግ ነው፡፡ በተጨማሪም አባላቱ እና ጋዜጠኞች የሚደርስባቸውን ማንኛውንም አይነት ጥቃት እንዲከላከሉ መደገፍ ፣ ጥቃቶችም ሲፈፀሙ የተጠቂዎች ድምፅ በመሆን መፍትሔ ለማስገኘት መሞገት እንዲሁም ሙያዊ ብቃት እንዲሻሻል ተግቶ መስራት ናቸው፡፡

አባልነት
የጋዜጠኞች ደህንነት
ይደግፉን
ይርዱ

በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ከፍተኛውን ሚና የሚጫወተው ነፃ ፣ ገለልተኛ እና የታመነ የመረጃ ፍሰት ያለው የመገናኛ ብዙሃን መፍጠር የኢትዮጵያ አርታኢያንን በአንድ መድረክ እንዲሰባሰቡ ያስቻላቸው ራዕይ ነው፡፡ ይህ ታላቅ ራዕይ የወለደው ኢአማ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ላይ ወሳኙን ኃላፊነት የተሸከሙት አርታኢያን መሰባሰቢያ ጥላ በመሆኑ ከፍተኛ ኩራት ይሰማዋል፡፡

እርስዎም በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ መረጃን ለህዝብ በሚያደርሱ የህትመት ፣ የበይነ-መረብ እና የስርጭት ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ/የሰሩ አርታኢ ከሆኑ ፣ የዚህ ታላቅ አላማ ተጋሪ እንዲሆኑ በክብር እንጋብዝዎታለን፡፡

የጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ደህንነትን የተመለከቱ ጉዳዮች የኢአማ አንዱ እና ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡ ማህበራችን በጋዜጠኞች እና በመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ከሰብአዊ መብት ጥሰት ባሻገር የኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ የመገንባት ሂደት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያደርስ ያምናል፡፡

እርስዎም በጋዜጠኞች እና መገናኛ ብዙሃን ላይ ሲከሰት ያዩትን ወይም የሰሙትን የጥቃት አይነት በዚህ ቅፅ አማካኝነት ለኢአማ እንዲጠቁሙ በማክበር እንጠይቅዎታለን!

ግድያ ፤ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ፤ የመስሪያ ቦታ ማሸግ እና ፈቃድ ክልከላ ፤ ፆታዊ ጥቃት ፤ እስር ፤ እገታ ፤ በጋዜጠኞች እና በመገናኛ ብዙሃን ላይ በማህበራዊ ሚድያ እና በሌሎችም መንገዶች የሚደረጉ ማንቋሸሽ ፣ ዘለፋ ፣ ስም ማጥፋት ፣ ወዘተ… ፤ ጋዜጠኞች ስራቸውን በሚሰሩበት ወቅት የሚደርስባቸውን ማዋከብ እና የመሳሰሉት ክስተቶች ሲያጋጥምዎት ወይም ሲመለከቱ በዚህ ቅፅ አማካኝነት ለኢአማ ያድርሱ፡፡

የእርስዎ ድጋፍ ኢአማ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ የሙያ ስነ-ምግባራቸውን አክብረው በነፃነት እንዲሰሩ በሚያደርገው ጥረት ላይ የላቀ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በጋራ የተሻለ የመናገር ነፃነት እና የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ማድረግ እንችላለን፡፡

‐‐

አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ማንቂያዎች ተዘግበዋል

በሴት ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ዛቻ

‐‐

በሴት ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ዛቻ

በእስር ላይ ተከሰው ያሉ ጋዜጠኞች

‐‐

በእስር ላይ ተከሰው ያሉ ጋዜጠኞች