የኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን 2/3ኛ አባላቱ ከክልሎች የመጡ አባላትም ጭምር በተገኙበት ዛሬ ነሀሴ 7 2014 ዓ.ም በሳፋየር አዲስ ሆቴል አዲስ አበባ አካሂዷል። በጉባኤውም የ2014 የፕሮጀክት እንዲሁም የፋይናንስ አፈፃፀሙን ገምግሞ አፀድቋል። የመተዳደሪያ ደንቡንም ለአሰራር በሚያመች መልኩ አሻሽሏል። የነበሩ ድክመቶችን አስተካክሎ ጠንካራ ስራዎቹንም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠቅላላ ጉባኤው ወስኗል።