ኢአማ ምንድነው?
ኢአማ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ህግ መሰረት የተመዘገቡ እና በየጊዜው ዘገባዎችን ለህዝብ የሚያቀርቡ የህትመት ፣ የበይነ-መረብ እና የስርጭት መገናኛ ብዙሃን ውስጥ በሚሰሩ አርታኢያን የተመሰረተ የሙያ ማህበር ነው፡፡
ኢአማ የተቋቋመው በምን መነሻ ነው?
ኢአማ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ውስጥ ወሳኝ እና ጉልህ ሚና ያላቸው አርታኢያን በጋራ ባለመደራጀታቸው ይህንንም ተከትሎ ዋናዎቹ የጥቃት እና ተፅዕኖ ሰለባዎች እነሱ በመሆናቸው እና በአንድነት ተደራጅተው የራሳቸውንም ሆነ የዘርፉን ነፃነት ማስጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡
የኢአማ ገቢ ምንድነው?
ኢአማ ገቢው በዋናነት የአባላት መዋጮ ሲሆን ፣ በተጨማሪም ከግለሰቦች ፣ በሀገር በቀል እና በውጭ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ ስራዎቹን ያከናውናል፡፡
እንዴት የኢአማ አባል መሆን ይቻላል?
ማንኛውም አርታኢ ወይም በአርታኢነት ያገለገለ ግለሰብ የኢአማ አባል ለመሆን ይችላል፡፡ አባልነት በሁለት መንገዶች የተከፈለ ሲሆን እነዚህም መደበኛ አባል እና የክብር አባል ናቸው፡፡
አባልነትን በተመለከተ ዝርዝር መረጃን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡
ሌላ ተዛማጅ ጥያቄ ካለዎት በዚህ ያግኙን፡፡
ኢአማ የሚመራው በማን ነው?
በኢአማ ድርጅታዊ መዋቅር መሰረት የበላይ የሆነው አካል ጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡ ይህ ጉባኤ በዓመት አንድ ጊዜ የሚሰበሰብ ሲሆን መላው አባላቱን የያዘ ነው፡፡ የማህበሩን የስራ አፈፃፀም የሚከታተለው ደግሞ ዘጠኝ አባላት ያሉት የኢአማ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ ነው፡፡ የኢአማ ዋና ስራ አስኪያጅ እና ሌሎች ተቀጣሪ ሰራተኞች የማህበሩን የለት-ተዕለት ስራዎችን ይከውናሉ፡፡

Recent Updates